የጽሑፍ አስተያዬት ትንተና እና ንጽጽር ጥናት (Sentiment Analysis)

በዚህ ጥናት፤ የተለያዩ ጽሑፎች የሚያመላክቱትን አስተያዬቶች (የስሜት ትንተና - sentiment/opinion) ይገመግማሉ። የስሜት ትንተና ማለት ጽሑፎችን ገምቢ፣ አፍራሽ፣ ገለልተኛ ወይም ቅልቅልቅ መሆናቸውን ለመለየት የሚያስችል የአሠራር ቴክኒክ ነው፡፡ ጥናቱ በተለይ በማኅበራዊ ሜዲያ የሚለቀቁ ጽሑፎች ገንቢ ወይም አፍራሽ መሆናቸውን ገምግሞ የተለያዬ ምልከታን ለመውሰድ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ ጥናት ለአማርኛ ቋንቋ የመጀመሪያ የሆነውን የስሜት/ሐሳብ ትንተናን የሚመረምር ዳታ ለማዘጋጀት የታቀደ ነው።

ይሳተፉ! ከአስር ብር ጀምሮ የሞባይል ካርድ ይሸለማሉ!

በጥናቱ ለመሳተፍ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡ t.me/Hizevbot

ስለዚህ ፕሮጄክት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወይም ጥያቄ ካለዎት በዚህ ኢ-ሜይል፣ ​hizkiel.alemayehu@studio.unibo.it​ ላይ ይጻፉልን ። በተጨማሪ ስለ ቅጹ አሞላል ለመረዳት ይህንን የዩቱዩብ “ቱቶርያል” ከፍተው ይመልከቱ Youtube። ይህ ሰርቬይ አግባብ ያልሆኑ ቃላት ወይም ንግግሮች ሊኖሩት ይችላል። ከ18 አመት በታች ከሆኑና ተገቢ ያልሆኑ ንግግሮችን ማየት ካልፈለጉ /end የሚለውን ተጭነው ይውጡ። በተጨማሪም በመጠይቁ ላይ የተቀመጡት ጽሁፎች ከቲዊተር የተሰበሰቡና የተመራማሪዎቹን ሀሳብ የማይወክሉ መሆኑን እንገልጻለን። በዚህ የምርምር ፕሮጀክት ውስጥ ያለዎት ተሳትፎ ሙሉ በእርስዎ ሙሉ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው። ምላሾችዎ ምሥጢራዊ እና ስም አልባ ሆነው ይቀመጣሉ። በዚህ ጥናት ላይ የሚመልሷቸው መልሶች እና የእርስዎ ማንነት ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው አይሰጡም። ይህ የጥናት እና የምርምር ፕሮጀክት በሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ (Universität Hamburg, LT Group) እና በቦሎኛ ዩኒቨርሲቲ (Università di Bologna) ትብብር የሚከናወን ነው።

ለትብብርዎ እናመሰግናለን!

ማስታወሻ፣ ስለሽልማቱ አሰጣጥ፦ ሽልማቱ የሚሰጠው ከ50 በላይ ጥያቄዎችን በትክክል ሲመልሱ ነው። ለማሸነፍ የሚያበቃዎትን ያህል ከሞሉ በኋላ፣ ወዲያውኑ የሞባይል ካርድ ይላክለዎታል።

ምሳሌዎች

ጽሁፍ አስተያዬት
ቋሚ ኮሚቴው የመንግስት ልማት ድርጅቶች እየተንከባለሉ የመጡ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ አሳሰበ ገለልተኛ
ፍትህ በሌለበት ሀገር ደሞክራሲ አለ ማለት ህዝብን መዋሸት ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቀበሌ ሊቀመንበር እስከ ምንስቴር ያለው አመራር ቅናተኛና ቅመኛ ነው፤ አፍራሽ
ሱፐር ስፖርት ስመጥር የስፖርት ጋዜጠኞችን ወደ ኮሜንታተር ፖናሉ በይፋ ቀላቅሏል። ገምቢ
በ 28ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ እድል ና አቶ በረከት አልተገናኝቶም አፍራሽ
ቡድኑ ያለበት ሁታ አሳሳቢ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ጠንካራ ስብእና ስላለው ችግሩን ያቀለዋል ቅልቅል
ጠንካራ ባህል ያለው ፣ መልካም ፣ ብልህ ፣ ጥበበኛ እንዲሁም ባለፀጋ ህዝብ ነዉ, ገምቢ